ከወንድ በላይ ተደባዳቢ ነበርኩኝ || ወደ ታንዛኒያ በየዋነቴ ተሸጥኩኝ || እኔ ወደኩኝ እነሱ አለፉ! || ENGIDAWORK ||እንተንፍስ #34

Manyazewal Eshetu

ባለታርካችን ከኢትዮጲያ ወደ ታንዛኒያ ተሽጣለች:: ጅማ ውስጥ ማንም የማይደፍራት ተደባዳቢ ነበረች:: አባቷን አታውቀውም:: እናቷ ስትሞት ታላቋ ትምህርት አቁማ ካፌ እየሰራች እሷን ማስተማር ጀመረች:: እያደገች ስትመጣ ግን ፈነዳች:: ከጏደኞቿ ጋር መቃም መጠጣት ማጨስ ጀመረች:: በወቅቱ ጅማ ውስጥ ዝነኛ የቡድን ጥል መሪ ሆነች:: የታክሲ ሹፌር አግብታም ወለደች::ትዳሩንም አፈረሰች:: ከቤተሰቦቿ ጋር ተጣልታ ወደ አዲስ አበባ መጣች::በምትሰራበት መስርያ ቤት